Saturday, June 14, 2025

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeዘገባዎችአራት ኪሎለመፈንቅለ መንግሥት ዓላማ የተከማቸ የጦር መሳሪያ አለ በሚል በአዲስአበባ ከተማ ፍተሻ ሊደረግ...

ለመፈንቅለ መንግሥት ዓላማ የተከማቸ የጦር መሳሪያ አለ በሚል በአዲስአበባ ከተማ ፍተሻ ሊደረግ ነው። 

ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ዞብል ፖስት ዜና!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ለመፈንቅለ መንግሥት የተዘጋጀ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ክምችት አለ መባሉን ተከትሎ፣ በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች ፍተሻ ሊያደርግ ነው።

ፖሊስ ይሄንን ፍተሻ ለማድረግ የወሰነው፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ክምችት አለ መባሉን ተከትሎ መሆኑን ለዞብል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ በከተማዋ “የጦር መሳሪያ ክምችት አለባቸው የተባሉ ቦታዎችን ለይቻለሁ” ማለቱ ተሰምቷል። ይሁንና ፖሊስ ፍተሻ የሚያደርግባቸውን አካባቢዎች ለጊዜው ምስጢራዊ እንዲሆን አድርጓል ነው የተባለው።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ኮሚሽነር ጄኔራል ደምመላሽ ገብረሚካኤል፣ ከሁለት ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የድሮን ቅኝት እናደርጋለን ማለታቸው ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፍተሻ የሚያደርገው በከተማዋ የመፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ እንቅስቃሴ አለ በሚል ስጋት እንደሆነ፣ ለመፅሔታችን የደረሰው መረጃ ያሳያል። ፖሊስ በከተማዋ አለ የተባለው የጦር መሳሪያ ክምችት “የመፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ የታቀደ ነው” ማለቱ ተሰምቷል።   

በፍተሻው በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ኤርትራውያን እና የአማራ ተወላጆች ዋነኛ ኢላማ ይሆናሉ መባሉን፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዞብል ፖስት ገልፀዋል።

ፍተሻውን በማስመልከት፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ለተለያዩ የዓለምአቀፍ ተቋማት እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቀደም ብሎ ደብዳቤ ማስገባቱን፣ መቀመጫውን በከተማዋ ያደረገ አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ለዞብል ፖስት ገልጿል።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች