Wednesday, June 25, 2025

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeዘገባዎችአራት ኪሎለከንቲባ አዳነች አቤቤ ሽልማት ያበረከተው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር የዲሲፕሊን እርምጃ ተወሰደበት።

ለከንቲባ አዳነች አቤቤ ሽልማት ያበረከተው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር የዲሲፕሊን እርምጃ ተወሰደበት።

ሰኔ 18/2017 ዓ.ም–ዞብል ፖስት ዜና!

የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በቅርቡ የከተማዋ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ምስል በትልቁ አዘጋጅቶ ለከንቲባዋ በሽልማት መልክ ማበርከቱ ይታወሳል።

ሽልማቱን ለከንቲባዋ ካበረከቱት ግለሰቦች መካከል አንደኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር በፓርቲው በተላለፈው ትዕዛዝ መሠረት የዲሲፕሊን እርምጃ እንደተወሰደባቸው ለዞብል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።

ሽልማቱን ለከንቲባ አዳነች አቤቤ ማበርከታቸውን ተከትሎ የዲሲፕሊን እርምጃ የተወሰደባቸው ግለሰብ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አመራር የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አበበ ናቸው።

የመኢአድ አመራር የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ለከንቲባዋ ሽልማት ማበርከታቸውን ተከትሎ፣ ፓርቲው በእኚሁ አመራር ላይ የእርምት እርምጃ ማስተላለፉን ለዞብል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።

የመኢአድ አባላትና ደጋፊዎች በፓርቲው አመራር በኩል ለከንቲባ አዳነች አቤቤ የተበረከተላቸው ሽልማት ምንን በማስመልከት እንደሆነ እንደማያውቁ እና አመራሩ ለከንቲባዋ ሽልማት ማበርከታቸው ድርጅታችንን አይወክልም ማለታቸውን ዞብል ፖስት ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ሰምቷል።   

የፓርቲው አመራሮችና አባላት የከንቲባ አዳነች ምስል በትልቁ ታትሞ በፓርቲው አመራር አቶ ሙሉጌታ በኩል ለከንቲባዋ በሽልማት መልክ ሲበረከት በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር መመልከታቸውን እና ድርጊቱ የድርጅቱን መላ አባላት እና ደጋፊዎች እንዳስቆጣ አንድ የፓርቲው አባል ለዞብል ፖስት ገልፀዋል።

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ከሦስት አሥርት ዓመታት በላይ በሰላማዊ ትግል በኢትዮጵያ ፖለቲካ ሲሳተፍ የቆዬ ሲሆን፣ ድርጅቱ ከሰሞኑ የፓርቲው አመራር የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አበበን ድርጊት ተከትሎ ከአመራርነት ለማገድ ውሳኔ ማሳለፉን ለመጽሄታችን የደረሰው መረጃ ያሳያል።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች