Tuesday, June 24, 2025

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeዘገባዎችአራት ኪሎስምረት ፓርቲ በአማራ ግዛቶች የመስራች አባላት ምልመላና ምዝገብ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሯል ተባለ። 

ስምረት ፓርቲ በአማራ ግዛቶች የመስራች አባላት ምልመላና ምዝገብ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሯል ተባለ። 

ሰኔ 17/2017 ዓ.ም–ዞብል ፖስት ዜና!

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ፣ በአማራ የተለያዩ ግዛቶች የመስራች አባላት ምልመላ እና ምዝገባ ለማካሄድ እንቅስቃሴ መጀመሩን ለመፅሔታችን የደረሰው መረጃ ያሳያል።

ስምረት ፓርቲ በራያ፣ ጠለምት፣ እና ኮረም አካባቢዎች የመስራች አባላትን ምዝገባ ለማካሄድ እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን፣ ሁኔታውን ተከትሎ ፓርቲው ከአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው ዞብል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።

ፓርቲው የመስራች አባላትን ምልመላ እና ምዝገባ አደርጋለሁ ያለባቸው አካባቢውዎች ተቃውሞ ያስነሱት “ስምረት የትግራይ ፓርቲ ነው እኛን አይወክልም” በማለት እንደሆነ ለመፅሔታችን የደረሰው መረጃ ያሳያል።

የአቶ ጌታቸው ረዳ ስምረት ፓርቲ የመስራች አባላት ምዝገባን ለማድረግ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ተቃውሞ ገጥሞታል የተባሉት የራያ፣ ኮረም፣ እና ጠለምት አካባቢዎች የአማራ ህዝብ ለዘመናት የወሰንና የማንነት ጥያቄ የሚያነሳባቸው አካባቢዎች እንደሆኑ ይታወቃል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በህወሓት ውስጥ የተፈጠረውን ከፍተኛ መከፋፈል ተከትሎ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ስምረት ፓርቲን በከሃዲነት መፈረጃቸው እና “እርምጃ ይወሰድበት” ማለታቸው የሚታወስ ነው። 

አቶ ጌታቸው ረዳ ከህወሓት ወጥተው ስምረት ፓርቲን ከመሰረቱበት ጊዜ ወዲህ፣ የጌታቸው ረዳ ደጋፊዎች ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ የዞንና የወረዳ አመራሮች ከኃላፊነት እየተነሱ ይገኛል። ለአብነት ያህል “ደቡባዊ ዞን” ብለው የሚጠሩት አካባቢ አስተዳዳሪ አቶ ዝናቡ ደስታ በቅርቡ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል። 

ከትግራይ ክልል በህወሓት እየተገፋ ያለው የጌታቸው ረዳ ቡድን፣ ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ በትግራይ በኩል ገጥሞታል የተባለውን የፓርቲ መዋቅራዊ ክፍተት የአማራ ህዝብ የማንነትና ወሰን ጥያቄ በሚያነሳቸው አካባቢዎች ለሟሟላት እንቅስቃሴ መጀመሩ በአካባቢዎቹ ሌላ የውጥረት መንስኤ ይሆናል ተብሎ ተሰግቷል።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች