Monday, June 16, 2025

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeሀገራዊ ጉዳዮችህወሓት አዲስ ወታደራዊ አዛዥ ለመሾም ውሳኔ አሳለፈ።

ህወሓት አዲስ ወታደራዊ አዛዥ ለመሾም ውሳኔ አሳለፈ።

ሰኔ 6/2017 ዓ.ም- ዞብል ፖስት ዜና 

ህወሓት ከሰሞኑ አዲስ ወታደራዊ አዛዥ ለመሾም ውሳኔ ማሳለፉን ዞብል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለዞብል ፖስት ባደረሱት መረጃ መሰረት፣ ጄኔራል ዮሐንስን ወይም ጄኔራል ምግበን የትግራይ ወታደራዊ አዛዥ ለማድረግ ውሳኔ ላይ ተደርሷል።

የህወሓት አመራሮች ይሄንን ውሳኔ ያሳለፉት፣ በቅርቡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾሙት ጄኔራል ታደሠ ወረደ የትግራይ ወታደራዊ እና ሲቪል ስልጣንን አንድ ላይ አጣምረው መያዝ የለባቸውም በሚል እንደሆነ፣ ለመፅሔታችን በደረሰው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

ጄኔራል ታደሠ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት ባለፈው ሚያዚያ ወር ሲሆን፣ ሹመቱን ከተቀበሉበት ጊዜ አንስቶ የወታደራዊ መሪነቱን ለሌሎች የህወሓት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች እንዲያስረክቡ ከህወሓት ባለስልጣናት ከፍተኛ ውትወታ ሲደረግባቸው መቆየቱን ለመፅሔታችን የደረሰው መረጃ ያሳያል። 

ይሁን እንጅ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነት ይበቃሃል የተባሉት ጄኔራል ታደሠ ወረደ በበኩላቸው፣ ለትግራይ አዲስ ወታደራዊ አዛዥ ለመሾም የቀረበውን ውሳኔ ውድቅ ማድረጋቸው ተሰምቷል።

የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሆነው የተሾሙት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነታቸው የተነሱት በተመሳሳይ የህወሓት ውስጣዊ መገፋፋት ምክንያት መሆኑ የሚታወስ ነው።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች