Friday, June 6, 2025

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeሀገራዊ ጉዳዮችሱዳን ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ገብተዋል ተባለ።

ሱዳን ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ገብተዋል ተባለ።

በሱዳን ብሉናይል ግዛት፣ ለወራት ወታደራዊ ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ በቁጥር በርከት ያሉ ታጣቂዎች፣ ከሰሞኑ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መዝለቃቸው ተሰምቷል።

ከብሉናይል ሰልጠነው የመጡት እነዚህ ታጣቂዎች፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ተወላጆች መሆናቸውን፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የዞብል ፖስት የመረጃ ምንጮች አስረድተዋል።    

ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ዘልቀው የገቡት ታጣቂዎች ቁጥራቸው ወደ 170 የሚደርሱ መሆናቸውን፣ የዞብል ፖስት የመረጃ ምንጮች አያይዘው ገልፀዋል። “ይሄን ያህል ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ሲመጡ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት መረጃው አልነበረውም” ሲሉ የመረጃ ምንጫችን አክለው ገልፀዋል።

ከብሉናይል የሱዳን ግዛት ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ የተደረጉት 170 ያህል የጉሙዝ ታጣቂዎችን፣ በስልጠና፣ በቁሳቁስ፣ እና በጦርመሳሪያ አቅርቦት በኩል፣ የግብፅ ድጋፍ ሳይኖርበት እንደማይቀር የመረጃ ምንጫችን አክለው ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም፣ “የቤንሻንጉል ህዝቦች የነፃነት ንቃናቄ” የተሰኘው የታጣቂ ቡድን፣ በግብፅ ይደገፍ እንደነበር ይታመናል። ቡድኑ ባለፈው ዓመት ከክልሉ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራርሞ፣ ወደ ሰላም ተመልሷል መባሉ የሚታወስ ነው።  

ከሰሞኑ ከሱዳን ብሉናይል ግዛት ሰልጥነው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቀው የገቡት ታጣቂዎች፣ መተከል እና አካባቢውን ጨምሮ፣ በተለያዩ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ክፍሎች ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች