Saturday, May 9, 2026

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeሀገራዊ ጉዳዮችበአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የጥበቃ ሠራተኛ አቅራቢ ኤጀንሲዎች የጥበቃ ሠራተኞችን ከኦሮሚያ ክልል...

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የጥበቃ ሠራተኛ አቅራቢ ኤጀንሲዎች የጥበቃ ሠራተኞችን ከኦሮሚያ ክልል እንዲቀጥሩ እየተገደዱ መሆኑ ተነገረ። 

መስከረም 9/2018 ዓ.ም–ዞብል ፖስት ዜና!

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የጥበቃ ሠራተኛ አቅራቢያ ኤጄንሲዎች የጥበቃ ሠራተኞችን ከኦሮሚያ ክልል እንዲቀጥሩ እየተገደዱ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዞብል ፖስት ያደረሱት መረጃ ያሳያል።

በከተማዋ የጥበቃ ሠራተኞችን ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚያቀርቡ በርካታ ኤጄንሲዎች የሚገኙ ሲሆን፣ እነዚሁ ኤጀንሲዎች የጥበቃ ሠራተኞችን ከኦሮሚያ ክልል እንዲወስዱ የክልሉ መንግሥት እያስገደደ ነው ተብሏል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የጥበቃ ኤጄንሲዎች ለስራ ቅጥር ዝግጁ የሆነ የሰው ኃይል መልምሎ እያሰለጠነ እንደሚገኝ መረጃውን ለዞብል ፖስት ያደረሱት ምንጮች አያይዘው ገልጸዋል።

የጥበቃ ሠራተኛ አቅራቢ ኤጄንሲዎች በንግድ ተቋማት፣ በሲቪልና ግለሰብ ድርጅቶች፣ እንዲሁም በመኖሪያ አፓርታማዎች በጥበቃ ስራ የሚሰማሩ ሠራተኞችን ለደንበኞቻቸው እንደሚያቀርቡ ይታወቃል።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥትም የጥበቃ ሠራተኞችን በማሰልጠን እና ለቅጥር ዝግጁ በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ በስፋት አገልግሎት የሚሰጠውን ይሄንኑ ዘርፍ ለመቆጣጠር በስፋት አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል ተብሏል።

በተያያዘ ዜና የኦሮሚያ ክልል መንግሥት “ገዳ ልዩ የኮማንዶ ኃይል” የተሰኘ ራሱን የቻለ ልዩ ስልጠና የሚሰጠው ወታደራዊ ኃይል በአዲስ አበባ ከተማ ሊያሰማራ እንደሆነ ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል።

አሁን ደግሞ በከተማዋ የሚገኙ የሲቪል ጥበቃ ኤጄንሲዎች የኦሮሚያ ክልል የሚያሰለጥናቸውን የጥበቃ ሠራተኞች እንዲቀጥሩ ግዳጅ እንደተጣለባቸው ዞብል ፖስት ከመረጃ ምንጮቹ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ በሚገኙ ወረዳዎች የሚያካሂደው የፀጥታ ኃይል ስምሪት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ስለመምጣቱ መሰል እንቅስቃሴዎች እንደ ሁነኛ ማሳያ ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ።  

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች