Saturday, May 23, 2026

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeከዓለም ገፅአሜሪካ እና እስራኤል በጥምረት በኢራን ላይ ጥቃት መክፈታቸው ተነገረ።

አሜሪካ እና እስራኤል በጥምረት በኢራን ላይ ጥቃት መክፈታቸው ተነገረ።

የካቲት 21 2018 ዓ.ም ዞብል ፖስት ዜና!

በዛሬው ዕለት እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት መክፈታቸውን በርካታ የመገናኛ ብዙሃን የሁለቱን ሀገራት ባለሥልጣናት ጠቅሰው በመዘገብ ላይ ይገኛል።

በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን ላይ በተፈፀመ ጥቃት፣ የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ እና የበላይ ጠባቂ በሆኑት አያቶላህ አሊ ካህሚኒ መስሪያ ቤት አጠገብ ከፍተኛ ፍንዳታ መሰማቱ ተነግሯል።

አሜሪካ እና እስራኤል በጋራ ሆነው በኢራን ላይ ጥቃቱን መክፈታቸው የተነገረው፣ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል በተደረገው ድርድር የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደስተኛ አለመሆናቸውን ካስታወቁ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነው ተብሏል።

አሜሪካ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት፣ ጦሯን እና ተዋጊ አውሮፕላኖቿን ወደ መካከለኛው ምስራቅ አስጠግታ የነበረ ሲሆን፣ ይህ የአሜሪካ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በኢራን ላይ ጥቃት ሊፈፀም እንደሚችል ሁነኛ ማሳያ ነበር።

ይህንን ተከትሎ እስራኤል እና አሜሪካ በቅንጅት ሆነው በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን የጀመሩትን ጥቃት፣ ወደተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጭምር በማስፋፋት ተከታታይ የአየር ላይ ድብደባ እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል።

ጥቃቱ ከተጀመረበት ሰዓት ጀምሮ ባለው መረጃ፣ የኢራን ፕሬዝዳንት “መስዑድ ፔዜሽኪያን” መኖሪያ ቤት እና የደህንነት ዋና መሥሪያ ቤትን ጨምሮ በ30 የተለያዩ ኢላማዎች ላይ ተከታታይ ጥቃት መፈጸሙን የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

በሌሌ በኩል፣ በዛሬው ዕለት በአሜሪካ እና እስራኤል የተፈፀመውን የአየር ጥቃት ተከትሎ፣ ኢራን ብርቱ የተባለ የአጸፋ ጥቃት ለመሰንዘር እየተዘጋጀች መሆኑን፣ የሮይተርስ ዜና ወኪል የኢራን ባለሥልጣናት ነግረውኛል ሲል ዘግቧል።

እስራኤል አሁን ላይ የአየር ክልሏን ሙሉ በሙሉ መዝጋቷ የተነገረ ሲሆን፣ የድሮንና የሚሳኤል ጥቃቶች ከኢራን በኩል ሊፈፀሙብኝ ይችላሉ በሚል ስጋት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመላው እስራኤል መታወጁም ተሰምቷል።

የእስራኤል መከላከያ ኃይል በእስራኤል ግዛቶች “ሳይረን” የተባለው የአደጋ ጊዜ ደወል ድምፅ መሰማቱን ያስታወቀ ሲሆን፣ ዜጎች ከጥቃት ጥበቃ ወደሚደረግባቸው ቦታዎች እንዲጠለሉ ወደ ሞባይል ስልኮቻቸው የቅድመ ጥንቃቄ መመሪያ ተላልፏል ብሏል።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች