Saturday, May 23, 2026

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeሀገራዊ ጉዳዮችበሩሲያ እና ዩክሬን መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ከሩሲያ ጎን ሆነው የሚዋጉ ኢትዮጵያውያን...

በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ከሩሲያ ጎን ሆነው የሚዋጉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ”1,800″ ማለፉ ተነገረ።

መጋቢት 13 2018 ዓ.ም–ዞብ ልፖስት ዜና!

በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት አራተኛ ዓመቱን የተሻገረ ሲሆን፣ ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከሩሲያ ጎን ሆነው በቅጥረኛ ተዋጊነት እየተሳተፉ እንደሚገኝ ዞብል ፖስት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

ለሩሲያ በተዋጊነት የሚመለመሉ ኢትዮጵያውያን አብዛኛዎቹ ከአማራ እና ከትግራይ ክልሎች እንደሆነ መጽሔታችን ያገኘው መረጃ የሚያሳይ ሲሆን፣ ባለፉት አራት ዓመታት ከ1 ሺህ 8 መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሩሲያ ጎን ሆነው በጦርነቱ መሳተፋቸው ተነግሯል።

አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ለሩሲያ ለመዋጋት የተፈራረመ ኢትዮጵያዊ ለዞብል ፖስት እንደገለፀው፣ ከትውልድ ቀየው ከአማራ ክልል ወደ ሩሲያ ለመጓዝ በቅድሚያ 800 ሺህ የሩሲያ ሩብል ወይም 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ገደማ እንደተከፈለው የገለፀ ሲሆን፣ በየወሩ ደግሞ 200 ሺህ የሩሲያ ሩብል ከሩሲያ መንግሥት እንደሚከፈለው አሳውቋል።

ግለሰቡ አክሎም ከሩሲያ ጎን ሆነው የሚዋጉ ኢትዮጵያውያን ቁጥራቸው ከ1 ሺህ 8 መቶ በላይ መድረሱን የጠቆመ ሲሆን፣ ከትግራይ ክልል ውቅሮ አካባቢ፣ ከኦሮሚያ ክልል ባሌ ሮቤ አካባቢ፣ እንደዚሁም ከኢትዮጵያ መንግሥት ፀጥታ መዋቅር ከድተው ለቅጥረኛ ተዋጊነት ወደ ሩሲያ የሄዱ ኢትዮጵያውያንን እንደሚያውቅ አያይዞ ገልጿል።

ኢትዮጵያውያኑ ለቅጥረኛ ተዋጊነት የሚመለመሉት በራሳቸው ፈቃድ እና የሦስተኛ ወገን ተፅዕኖ ሳይኖርባቸው እንደሆነ የተነገረ ሲሆን፣ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በምታደርገው ጦርነት ሲሳተፉ ግን የሩሲያን ሕግ ሙሉ በሙሉ ለመተግበር እንደሚገደዱ ታውቋል።

እንደ ዞብል ፖስት የመረጃ ምንጭ በሀገር ውስጥ የምልመላ እና የጉዞ ሂደቱን በማሳለጥ ረገድ የሚሳተፉ የተለያዩ አካላት የሚሳተፉ ሲሆን፣ የመንግሥት ፀጥታ መዋቅር ባለሥልጣናት ጭምር በቀጥታ ይሳተፋሉ ተብሏል።

መረጃውን ለዞብል ፖስት ያደረሰው ለሩሲያ በተዋጊነት የተሰለፈው ኢትዮጵያዊ እንደገለፀው፣ ቤተሰቦቹን ለማኖር ሲል፣ እንደዚሁም በኢትዮጵያ ባለው የሠላም እጦት እና ከፍተኛ የኑሮ ውድነት የተነሳ ለሩሲያ ቅጥረኛ ተዋጊ ለመሆን መወሰኑን አያይዞ ገልጿል።

በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ከሩሲያ ጎን ሆነው ለመዋጋት ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተነስተው ወደ ሩሲያ የሄዱ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የአውደ ውጊያ ግንባሮች መመደባቸው መረጃውን ከሩሲያ ለዞብል ለዞብል ፖስት ያደረሰን ኢትዮጵያዊው የሩሲያ ቅጥረኛ ተዋጊ አስረድቷል።

ለሩሲያ ለመዋጋት ወደ ጦርነት ግንባር የተጓዘው ኢትዮጵያዊ እንደገለፀው፣ በቅጥረኛ ተዋጊነት ወደ ሩሲያ ምድር የተጓዙ ኢትዮጵያውያን በጦርነት ጊዜ ህይወታቸው ቢያልፍ “እንደዬ ሐይማኖታቻው ስነ-ስርዓት በተመደቡበት የሩሲያ ክልል ቀብራቸው ይፈፀማል” ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተገናኘ፣ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከአራት ዓመታት በፊት ሲፈነዳ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከሩሲያ ጎን ተሰልፈው ለመዋጋት “ፍላጎት እንዳላቸው” ለማሳየት በሚያዚያ 2014 ዓመተ ምህረት በአዲስ አበባ የሩሲያ ኢምባሲ በር ተሰባስበው እንደነበር አይዘነጋም።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች