Monday, June 16, 2025

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeዜናዋና ዋና ዜናጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ታሰረ። 

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ታሰረ። 

ሰኔ 3/2017 ዓ.ም – ዞብል ፖስት ዜና

የኢትዮጵያ ኢንሳይደር የበይነ-መረብ ሚዲያ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ እሁድ ሰኔ 1 ቀን፤ 2017 በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋሉን ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን በዛሬው ዕለት ባወጠው መግለጫ አሳውቋል።

ጋዜጠኛ ተስፋለም በአዲስ አበባ ግዮን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ እያለ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋሉን፣ ጋዜጠኛው በመሰረተው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በይነ-መረብ ሚዲያ ላይ በወጣው መግለጫ ለማወቅ ተችሏል።

ጋዜጠኛው በፀጥታ ኃይሎች ከተወሰደ በኋላ በዛኑ ዕለት ሌሊቱን እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ሕንፃ ውስጥ ወንበር ላይ እንዲያድር መደረጉን፣ ሐቅ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባወጣው መግለጫ አያይዞ ገልጿል።

ተስፋለም በታሰረ በማግስቱ ሰኞ ሰኔ 2 ቀን፤ 2017 ቄራ አካባቢ ወደሚገኝ የፖሊስ መምሪያ ተወስዶ አንድ ቀን ካሳለፈ በኋላ፣ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 3 ቀን፤ 2017 በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ቂርቆስ ምድብ ችሎት ቀርቦ ነበር።

ፍርድ ቤቱ ተስፋለም በ15,000 ብር ዋስትና እንዲፈታ ወስኖ የነበረ ቢሆንም፣ ለዋስትና የተጠየቀው ገንዘብ ከተከፈለ በኋላ ፖሊስ በቃል ይግባኝ እንደሚጠይቅ በመግለፁ ምክንያት ጋዜጠኛው እስካሁን ሳይለቀቅ መቅረቱ ተገልጿል።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች