Tuesday, June 24, 2025

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeዜናዋና ዋና ዜናየቀድሞው የደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሠፋ የሚገኙበት ስብሰባ ሊካሄድ ነው። 

የቀድሞው የደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሠፋ የሚገኙበት ስብሰባ ሊካሄድ ነው። 

ሰኔ 14/2017 ዓ.ም – ዞብል ፖስት ዜና!

የቀድሞው የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ የነበሩት አቶ ጌታቸው አሠፋ የሚገኙበት ስብሰባ በመጪው ሐምሌ ወር በአሜሪካ እና አውሮፓ ሊካሄድ እንደሆነ ዞብል ፖስት ከምንጮቹ ሰምቷል።

ስብሰባውን የሚያካሂደው “ፅምዶ” የተሰኘው በቅርቡ የህወሓት እና የኤርትራ የፖለቲካ ኃይሎች የፈጠሩት ጥምረት እንደሆነ ለመፅሔታችን የደረሰው መረጃ ያሳያል። ስብሰባውም በመጪው ሐምሌ ወር በአሜሪካ እና አውሮፓ የተለያዩ ከተሞች ይካሄዳል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በድብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን እና የኤርትራ ወታደራዊና ፖለቲካዊ መሪዎች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ እንዲሁም የዳያስፖራ አባላት የተገኙበት ስብሰባ በኤርትራ ተደርጎ እንደነበር የሚያሳዩ የተለያዩ መረጃዎች መውጣታቸው ይታወሳል።

በመጪው ሐምሌ ወር የቀድሞው የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ የነበሩት አቶ ጌታቸው አሠፋ ይገኙበታል ተብሎ የሚጠበቀው በአሜሪካ እና አውሮፓ ከተሞች ይካሄዳል የተባለው ስብሰባ፣ በቅርቡ በኤርትራ ተደርጎ ነበር የተባለው ስብሰባ አካል እንደሆነ ለዞብል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል። ስብሰባው በአሜሪካ እና አውሮፓ የሚኖረዉን ዳያስፖራ ተሳታፊ ለማድረገ ያለመ ነዉም ተብሏል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ከህወሓት የወጡ የፖለቲካ እና ወታደራዊ መሪዎች ቡድን ከዐቢይ አህመድ ጋር መስራት መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን፣ ሁኔታው የትግራይ ፖለቲካ በኢሳያስ አፈወርቂ እና በዐቢይ አህመድ እጅ መውደቁን ይጠቁማል።

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተፈጠረው መቃቃር ብዙ ሀገራዊ እና ቀጠናዊ ለውጦችን እያስከተለ ሲሆን፣ የህወሓትን ለሁለት መሰንጠቅን ተከትሎ የተፈጠሩ አንጃዎች ደግሞ የትግራይ ፖለቲካ ለዐቢይ አህመድ እና ኢሳያስ አፈወርቂ በአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ ፖለቲካ የኃይል ሚዛን ፉክክር ምቹ ሜዳ እየሆነ የመጣ ይመስላል።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች