Thursday, May 7, 2026

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeሀገራዊ ጉዳዮችየኢትዮጵያ ልማት ባንክ በብድር አቅርቦት ዙሪያ ከአማራ ባለሀብቶች ከፍተኛ ቅሬታ እየቀረበበት ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በብድር አቅርቦት ዙሪያ ከአማራ ባለሀብቶች ከፍተኛ ቅሬታ እየቀረበበት ነው።

ሐምሌ 8/2017 ዓ.ም–ዞብል ፖስት ዜና! 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በብድር አቅርቦት እና ተያያዥ ጉዳዮች ከአማራ ባለሀብቶች ተደጋጋሚ ቅሬታ እየቀረበበት እንደሆነ ዞብል ፖስት ከባንኩ ሠራተኞች ያገኘው መረጃ ያሳያል።

ከዚህ ቀደም ከልማት ባንኩ ብድር ያገኙ ባለሀብቶች የዐቢይ አህመድ መንግሥት በአማራ ላይ የከፈተውን ጦርነት ተከትሎ፣ በንግድ እንቅስቃሴዎቻቸው ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል እየገጠማቸው እና ለወሰዱት ብድር የተሰጣቸው የእፎይታ ጊዜ ያለምንም ስራ እና ገቢ እየተጠናቀቀ ስለመሆኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ይሄንን ተከትሎ ባለሀብቶቹ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የወሰዱትን ብድር ለመመለስ መቸገራቸውን ጠቅሰው ባንኩ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጣቸው የሚያቀርቡት ጥያቄ ውድቅ እየተደረገባቸው ስለመሆኑ የደረሰን መረጃ ያመላክታል። 

ከልማት ባንኩ ብድር የወሰዱ ባለሀብቶች በጦርነቱ ምክንያት የስራ እንቅስቃሴያቸው በከፍተኛ ሁኔታ በመቀዛቀዙና ገቢያቸው በመቀነሱ ምክንያት ከልማት ባንኩ የወሰዱትን ብድር ለመመለስ የተቸገሩ ሲሆን፣ ባንኩ ሁኔታውን ከግምት ውስጥ እንዲያስገባ ለሚቀርብለት ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ እየሰጠ አለመሆኑን ለመፅሔታችን የደረሰው ዜና ያሳያል። 

ከዚህም በተጨማሪ የአማራ ባለሀብቶች ብድር ለመጠየቅ ፕሮፖዛላቸውን በሚያስገቡበት ወቅት ብድር የመመለስ ዕድላችሁ ጠባብ ነው በሚል በባንኩ ባለስልጣናት የብድር ጥያቄያቸው ውድቅ እንደሚደረግባቸው ለዞብል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ በአማራ ክልል የተጀመሩ ወይም ለመጀመር የታሰቡ ፕሮጀክቶች የብድር አቅርቦት እንዳያገኙ በተጠና መልኩ የማስተጓጎል ተግባር እየተፈፀመ ስለመሆኑ የመረጃ ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች