Saturday, May 9, 2026

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeከዓለም ገፅ"በአሜሪካ እና ኤርትራ መካከል በመከባበር እና ሀቀኝነት ላይ የተመሰረት ግንኙነት ለመፍጠር ዝግጁ...

“በአሜሪካ እና ኤርትራ መካከል በመከባበር እና ሀቀኝነት ላይ የተመሰረት ግንኙነት ለመፍጠር ዝግጁ ነን” ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ!

ሐምሌ 25/2017 ዓ.ም–ዞብል ፖስት ዜና! 

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኤርትራው አቻቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ደብዳቤ መላካቸውን የኤርትራው የኢንፎርሜሽን ሚንስትር የማነ ገብረመስቀል በማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፃቸው ገልጸዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ለኢሳያስ አፈወርቂ በላኩት ደብዳቤ አስተዳደራቸው በአሜሪካ እና ኤርትራ መካከል በመከባበር እና ሀቀኝነት ላይ የተመሰረት ግንኙነት ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቀዋል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትናንትናውን ዕለት ለኢሳያስ አፈወርቂ በጻፉት ደብዳቤ “የባይደን አስተዳደር በዓለም ዙሪያ ያደረሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ እየቀለበሱ መሆናቸውን” አፅንኦት ሰጥተው ገልጸዋል ሲሉ የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩ የማነ ገብረመስቀል በማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባሳለፍነው ህዳር ወር ከኤርትራው አቻቸው ለተላከላቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ምስጋና በማቅረብ፣ አስተዳደራቸው  “በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር አካባቢ ሰላምንና ልማትን ለማሻሻል የሚያስችል በሀቀኝነትና መከባበር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት በሁለቱ ሀገራት መካከል መልሶ እንዲፈጠር ለማድረግ አስተዳደራቸው ዝግጁ መሆኑን በደብዳቤያቸው ገልጸዋል ሲሉ የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩ አያይዘው ጠቁመዋል።

የማነ ገብረመስቀል አክለውም ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ባለፈው ህዳር ላይ “ዓለም ከመቼውም ጊዜ በላይ ለሠላም በሚጨነቅበት ወሳኝ ወቅት፣ ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው እንኳን ደስ አለዎት” ማለታቸውን በመጠቆም፣ በኤርትራና አሜሪካ መካከል ገንቢና ፍሬያማ የትብብር የግንኙነት ምዕራፍ እንደሚከፈት ተስፋ ማድረጋቸውን አውስተዋል።

በኤርትራ እና አሜሪካ መካከል ከፍተኛ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ውጥረት ሰፍኖ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ ሁለቱ መሪዎች የተላላኳቸው መልዕክቶች የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ጤናማ በሆነ መልኩ እንደ አዲስ ሊጀመር ሰለመሆኑ አመላካች ለውጥ ተደርጎ ሊታይ ይችላል።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች