Friday, October 23, 2026

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeዘገባዎችአራት ኪሎብርጋዲየር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ መፅሐፉን ሊያስመርቅ ነው።

ብርጋዲየር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ መፅሐፉን ሊያስመርቅ ነው።

ነሐሴ 7/2017 ዓ.ም–ዞብል ፖስት ዜና! 

በአማራ ሕዝብ ላይ የታወጀውን ጦርነት ከፊት ሆነው ከሚመሩት ወታደራዊ አመራሮች አንዱ የሆኑት ብርጋዲየር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ ከሰሞኑ መፅሐፍ ሊያስመርቅ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዞብል ፖስት ገልጸዋል።

የጄኔራሉ መፅሐፍ “የአማራ ሕዝብ ፈተናዎች እና የመውጫ ብልሃቶች” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ እንደሆነና በመጪው ነሐሴ 10 በደሴ ከተማ ሉሲ ሆቴል እንደሚመረቅ መረጃውን ያደረሱን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ባለሀብቶች እና የደሴ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ባለሥልጣናት የከተማው ሕዝብ የብርጋዲየር ጄኔራል ዘውዱን መፅሐፍ እንዲገዛ ከወዲሁ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

ከአብራኩ በወጡ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ መሪዎች እየተመራ ሁለት ዓመታትን የተሻገረው የአማራ ጦርነት የሕዝቡ ወቅታዊ ፈተና ሲሆን፣ ጦርነቱን ከፊት ሆነው ከሚመሩት የአማራ ተወላጆች አንዱ የሆኑት ብርጋዲየር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ የአማራን ሕዝብ ፈተናዎች ለይቼበታለሁ ባሉት መፅሐፍ ውስጥ “ራሳቸውን የፈተናው አካል ወይስ የመውጫ ብልሃት አድርገው ያቀርባሉ?” የሚለው ጉዳይ ተጠባቂ ይሆናል።

ፈተና ገጥሞታል ላሉት የአማራ ሕዝብ የመውጫ ብልሃት እጠቁማለሁ ብለው መፅሐፍ የፃፉት ጄኔራል ዘውዴ ሰጥአርጌ የሚያገለግሉት የዐቢይ አህመድ መንግሥት ችግሮችን ሁሉ በጦርነት እፈታለሁ የሚል፣ ለተቃውሞ ድምጾች ሁሉ ጦር የሚያዘምትና ንፁሐንን በድሮንና ከባድ መሳሪያ የሚጨፈጭፍ መሆኑ ጄኔራሉን ትዝብት ላይ የሚጥላቸው ይሆናል።  

ብርጋዲየር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ በአማራ ሕዝብ ላይ የታወጀውን ጦርነት ከፊት ሆነው ከሚመሩት የዐቢይ አህመድ ታማኝ ጄኔራሎች መካከል አንዱ ሲሆን፣ ከደሴ እስከ አባይ ሸለቆ፣ ዋግህምራ፣ እና ጨጨሆ ባለው ቀጠና የተሰማራው የ801ኛ ኮር ዋና አዛዥ ነው።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች