Sunday, May 17, 2026

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeሀገራዊ ጉዳዮችበሸገር ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በአማርኛ ቋንቋ እንዳያስተምሩ ተከለከሉ። 

በሸገር ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በአማርኛ ቋንቋ እንዳያስተምሩ ተከለከሉ። 

ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም–ዞብል ፖስት ዜና!

በሸገር ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በአማርኛ ቋንቋ እንዳያስተምሩ የከተማ አስተዳደሩ የክልከላ ውሳኔ ማስተላለፉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዞብል ፖስት ገልጸዋል።

የሸገር ከተማ የተመሰረተው የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በርካታ መስጊዶችን እና ቤተክርስቲያናትን፣ እንዲሁም ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ቤቶችን አፍርሶ እና ከአምስት መቶ ሺህ በላይ ዜጎችን አፈናቅሎ መሆኑ የሚታወስ ነው።

የሸገር ከተማ አስተዳደር የአማርኛ ቋንቋ በከተማው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንዳይሰጥ ያሳለፈው ውሳኔ ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን መረጃውን ለዞብል ፖስት ያደረሱት ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

የመጽሔታችን የመረጃ ምንጮች እንደገለፁት በሸገር ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት ላይ እንዳይውል የከተማ መስተዳድሩ ክልከላ ያደረገው ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰመስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተላለፈው ቀጥተኛ ትዕዛዝ መሆኑ ተነግሯል።

ይሄንን ተከትሎ ከዚህ ቀደም ትምህርት በአማርኛ ቋንቋ ይሰጡ የነበሩ ትምህርት ቤቶች በኦሮምኛ ቋንቋ ብቻ እንዲያስተምሩ ውሳኔ የተላለፈ ሲሆን፣ ይሄንን የማያደርጉ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ይደረጋል መባሉን ለዞብል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።

ከዚህም በተጨማሪ፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ከዚህ በፊት በአማርኛ ቋንቋ የተማሩ ህፃናት በመጪው መስከረም ወር በሚጀመረው የትምህርት ዘመን ከእንደገና ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንዲመዘገቡ እና በኦሮምኛ ቋንቋ እንዲማሩ ይደረጋል ተብሏል።

አዲስ አበባን ዙሪያዋን አጥሮ እንዲመሰረት የተደረገው የሸገር ከተማ ሙሉ በሙሉ ኦሮሞን መመሰል አለበት በሚል በርካታ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ያልሆኑ ዜጎች ከአካባቢው በግድ እንዲፈናቀሉ እና ሀብት ንብረታቸው በመንግሥት እንዲወረስ መደረጉ አይዘነጋም።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች