Friday, May 8, 2026

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeሀገራዊ ጉዳዮችየኬኒያ የፀጥታ ኃይሎች የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው በርካታ ኢትዮጵያውያንን አግተው መውሰዳቸው ተነገረ።

የኬኒያ የፀጥታ ኃይሎች የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው በርካታ ኢትዮጵያውያንን አግተው መውሰዳቸው ተነገረ።

ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም–ዞብል ፖስት ዜና! 

የኬኒያ የፀጥታ ኃይሎች የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው ኢትዮጵያውያንን አግተው መውሰዳቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዞብል ፖስት ገልጸዋል።

የኬንያ የፀጥታ ኃይሎች ከጥቂት ቀናት በፊት ኬኒያንና ኢትዮጵያን የሚያዋስነውን ድንበር አቋርጠው ከገቡ በኋላ በአዋሳኝ ስፍራዎች የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያንን አግተው መውሰዳቸው ተነግሯል።

የዞብል ፖስት የመረጃ ምንጮች ለመጽሔታችን እንደገለጹት፣ የሀገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ በርካታ የኛንጋቶም ተወላጆች በኬኒያ ፀጥታ ኃይሎች ታግተው ተወሰድዋል ተብሏል። 

የኬንያ ፀጥታ ኃይሎች የኛንጋቶም ተወላጆችን አግተው በወሰዱበት ወቅት አርባ አምስት ኪሎ ሜትር ያህል የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው መግባታቸውን የመረጃ ምንጫችን አክለው ገልጸዋል።

በቱርካና ሐይቅ እና በኦሞ ወንዝ ዙሪያ በሁለቱ ሀገራት አዋሳኝ ስፍራዎች በሚገኙ አርብቶአደር ጎሳዎች መካከል በውሃ አጠቃቀም እና በግጦሽ መሬት አለመግባባቶች ምክንያት በተለያዩ ጊዜያት እገታ እና ባስ ሲልም ግድያን ያስከተሉ ግጭቶች ሲከሰቱ ይስተዋላል።  

በአካባቢው በዋናነት በዳሰነች ወረዳ ተመሳሳይ ችግሮች በተደጋጋሚ ሲከሰቱ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ከሰሞኑ ደግሞ በርካታ የኛንጋቶም ተወላጆች ታግተው የተወሰዱበት ክስተት ተፈጥሯል።

የኬኒያ የፀጥታ ኃይሎች አርባ አምስት ኪሎሜትር ያህል የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ኢትዮጵያውያንን አግተው ሲወስዱ በአካባቢው የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች እንዳልነበሩና ዜጎችን ከእገታ ማስጣል እንዳልተቻለ መረጃውን ለመጽሔታችን ያደረሱት ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያም ሆነ የኬኒያ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ያሉት ነገር ባይኖርም፣ የኬንያ የፀጥታ ኃይሎች የኢትዮጵያ ድንበር አቋርጠው እገታ መፈፀማቸውን የአካባቢው ምንጮች ለዞብል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።  

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች