Saturday, May 9, 2026

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeሀገራዊ ጉዳዮችየአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የኦሮምኛ ቋንቋ መምህራንን ወደ ሌሎች የስራ መደቦች...

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የኦሮምኛ ቋንቋ መምህራንን ወደ ሌሎች የስራ መደቦች እያዘዋወረ መሆኑ ተገለፀ።

መስከረም 5/2018 ዓ.ም ዞብል ፖስት ዜና! 

የአዲስ አበባ ከተማ መሥተዳድር ትምህርት ቢሮ ከዚህ ቀደም በኦሮምኛ ቋንቋ መምህርነት የስራ መደብ የቀጠራቸውን መምህራንን ወደ ሌሎች የስራ መደቦች እያዘዋወረ መሆኑን ለዞብል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።

እንደ ዞብል ፖስት የመረጃ ምንጮች የኦሮምኛ ቋንቋ መምህራን ወደ ሌሎች የስራ መደቦች እየተዘዋወሩ የሚገኙት መምህራኖቹ ቀድሞውንም ሲቀጠሩ በቁጥር መብዛታቸው ዋነኛው ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ መሥተዳድር ትምህርት ቢሮ የኦሮምኛ ትምህርት ክፍል መምሪያ ማቋቋሙን ተከትሎ በአንድ ትምህርት ቤት እስከ ስድስት የሚደርሱ የኦሮምኛ ቋንቋ መምህራን እንዲቀጠሩ ተደርጎ የነበረ ሲሆን፣ ሁኔታው የመምህራኑ ቁጥር ከፍ እንዲል ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

ይህንን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በኦሮምኛ ቋንቋ መምህርነት ተመድበው የነበሩ መምህራን አሁን ላይ ወደ ሌሎች የስራ መደቦች እየተዘዋወሩ መሆኑ ተነግሯል።

የኦሮምኛ ቋንቋ መምህራኖቹ የአዲስ አበባ ከተማን የፀጥታ መዋቅር እና የደኅንነት ስራን ጨምሮ በሌሎች የተለያዩ የመንግሥት ስራዎች እንዲመደቡ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ መሥተዳድር የሰራተኞች ቅነሳ ባደረገባቸው የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እነዚሁ የኦሮምኛ ቋንቋ መመህራን እንዲመደቡ ይደረጋል መባሉን የመረጃ ምንጫችን ለዞብል ፖስት አክለው ገልጸዋል።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች