Saturday, May 9, 2026

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeሀገራዊ ጉዳዮችአቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለዲፕሎማቲክ ማሕበረሰቡ ማብራሪያ ሰጡ። 

አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለዲፕሎማቲክ ማሕበረሰቡ ማብራሪያ ሰጡ። 

ሐምሌ 12/2017 ዓ.ምዞብል ፖስት ዜና! 

የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መስተዳድር ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከሰሞኑ የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ለዲፕሎማቲክ ማሕበረሰቡ ማብራሪያ መስጠታቸውን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ለዞብል ፖስት ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው አግኝተው ካነጋገሯቸው የውጭ ዲፕሎማቶች መካከል፣ የአውሮፓ ሕብረት አባል ሀገራት እና የአሜሪካ ተወካዮች የሚገኙበት ሲሆን፣ የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ለዲፕሎማቶቹ ማብራሪያ የተሰጠው በዚህ ሳምንት መጀመሪያ እንደነበር ለመጽሔታችን የደረሰው መረጃ ያሳያል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ለአውሮፓ ሕብረት እና የአሜሪካ ዲፕሎማቶች የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ ሲያስረዱ፣ የህወሓት ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራሮች የትግራይን ሕዝብ ወደ ዳግም ጦርነት ሊያስገቡት እየሰሩ እንደሆነ መግለጻቸውን ዞብል ፖስት ከዲፕሎማቲክ ምንጮቹ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

በውይይቱ ወቅት የአውሮፓ ሕብረት እና አሜሪካ ተወካዮች በብርጋዲየር ጄኔራል ገብረእግዚአብሔር በየነ መሪነት በአፋር ቀጠና ወታደራዊ ስልጠና እያደረገ ስላለው “የነፃ መሬት” ታጣቂዎች ወይም “የትግራይ ሠላማዊ ኃይል” አስመልክቶ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ አቶ ጌታቸው በበኩላቸው “ሁኔታው የሚያሳየው የትግራይ ሕዝብ ከህወሓት ሌላ አማራጭ ኃይል እንደሚፈልግ ነው” የሚል ምላሽ መስጠታቸው ተሰምቷል።

ከዚህ በተጨማሪ የህወሓት እና የኤርትራ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ መሪዎች የፈጠሩት ፅምዶ የተሰኘው ጥምረት፣ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ተጨማሪ የጦርነት ድግሥ ሊያስከትል እንደሚችል፣ አቶ ጌታቸው ረዳ ለዲፕሎማቲክ ማሕበረሰቡ አያይዘው ማስረዳታቸውን የመረጃ ምንጫችን አያይዘው ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ህወሓት ለአፍሪካ ሕብረት ከሰሞኑ ደብዳቤ መላኩ የተነገረ ሲሆን፣ ሕብረቱ ምርጫ ቦርድ የህወሓትን ሕጋዊ ሰውነት እንዲመልስ ጫና እንዲፈጥር መጠየቁ ተነግሯል። ከዚህ በተጨማሪም፣ “የአፍሪካ ሕብረት ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር ያወያየኝ” ሲል ህወሓት በደብዳቤው አክሎ መጠየቁን ለመጽሔታችን የደረሰው መረጃ ያሳያል።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች