Saturday, May 9, 2026

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeሀገራዊ ጉዳዮችበጋምቤላ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ። 

በጋምቤላ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ። 

ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም–ዞብል ፖስት ዜና! 

በጋምቤላ ክልል እና ከአራት ዓመታት በፊት በተመሰረተው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መካከል ግጭት መቀስቀሱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዞብል ፖስት ገልጸዋል።

ግጭቱ የተቀሰቀሰው በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ቦታ ሲሆን፣ የግጭቱ መንስኤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከአራት ዓመታት በፊት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ሲያከራክር የቆየ የድንበር ይገባኛል ውዝግብ እንደሆነ ለመጽሔታችን የደረሰው ዜና ያሳያል።

በሁለቱ ክልሎች መካከል ግጭት የተቀሰቀሰው በትናንትናው ዕለት ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም ሲሆን፣ የሁለቱ ወገን የፀጥታ ኃይሎች የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውንና በግጭቱ ንፁሃንን ጨምሮ የበርካቶች ህይወት ማለፉን የመረጃ ምንጫችን አክለው አስረድተዋል።

ግጭቱ የተቀሰቀሰው በጋምቤላ ክልል ልዩ ስሙ ዲማ ተብሎ በሚጠራውና ሁለቱን ክልሎች በሚያዋስነው ወረዳ አቅራቢያ ሲሆን፣ በሁለቱ ክልሎች የፀጥታ ኃይሎች መካከል የሰዎችን ህይወት የቀጠፈ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል።

በጋምቤላ ስር በሚገኘው የዲማ ወረዳ አቅራቢያ በሚገኙ ቀበሌዎች ላይ በሁለቱ ክልሎች መካከል የተነሳው የድንበር ይገባኛል ውዝግብ ወደ ግጭት ማምራቱን ተከትሎ በተደረገው የተኩስ ልውውጥ የፀጥታ ኃይሎች እና ንፁሐን ተገድለዋል።

በግጭቱ ከሁለቱም ወገኖች ያሉ የፀጥታ ኃይሎችን እና ንፁሐንን ጨምሮ በአጠቃላይ ሃያ አራት ሰዎች መገደላቸውን የመረጃ ምንጫችን ለዞብል ፖስት የገለጹ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች