Saturday, May 9, 2026

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeሀገራዊ ጉዳዮችበአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ባለሃብቶች የጌታቸው ረዳ እና የደብረፅዮን ቡድን በሚል ወደ...

በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ባለሃብቶች የጌታቸው ረዳ እና የደብረፅዮን ቡድን በሚል ወደ ግጭት እየገቡ መሆኑ ተነገረ።

መስከረም 30/2018 ዓ.ም–ዞብል ፖስት ዜና!

በህወሓት ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ባለሃብቶች የአቶ ጌታቸው ረዳ እና የደብረፅዮን ደጋፊዎች በሚል ለሁለት መከፈላቸውን ለዞብል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።

የህወሓት መከፋፈል በባለሃብቶች መቧደንን ከማስከተሉም በላይ በመካከላቸው ግጭት እስከመፈጠረ የደረሱበት ሁኔታ መኖሩን መረጃውን ያደረሱን ምንጮች አያይዘው ገልጸዋል።

በባለሃብቶቹ መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ተከትሎ ከአስመጪና ላኪ እስከ አምራች ድርጅቶች ድረስ በትግራይ ባለሃብቶች በሽርክና የሚንቀሳቀሱ የንግድ ስራዎች እስከመቆም እየደረሱ ነው ተብሏል።

የአቶ ጌታቸው ረዳ እና የደብረፅዮን ገብረሚካኤል ደጋፊ በሚል የተፈጠረው ፖለቲካዊ ልዩነት በመዲናዋ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆችን የማኅበራዊ ህይወት ግንኙነት እስከማቋረጥ ጭምር መድረሱ ተነግሯል።

እኒሁ ባለሃብቶች የጌታቸው እና የደብረፅዮን ቡድን በሚል ተከፋፍለው በተለያዩ ጊዜያት ስብሰባዎችን እስከማድረግ የደረሱ ሲሆን፣ በመካከላቸው የተፈጠረው ልዩነት ይበልጥ እየተካረረ መሄዱን መረጃውን ለመጽሔታችን ያደረሱት አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሆቴል ሥራ አስኪያጅ አያይዘው ገልጸዋል።

እንደ ዞብል ፖስት የመረጃ ምንጮች ከሆነ በባለሃብቶቹ መካከል እየተካረረ የመጣው መከፋፈል በምሽት ቤቶች ሽጉጥ እስከመማዘዝ የደረሰ ሲሆን፣ በያዝነው የመስከረም ወር ብቻ መሰል ድርጊቶች በቦሌ እና ሳር ቤት አካባቢዎች ሁለት ጊዜ መከሰታቸው ተሰምቷል።

በህወሓት ውስጥ የተፈጠረው ልዩነት ከአመራሮቹ አልፎ በንግዱ ማኅበረሰብ ጭምር እየተስተዋለ መምጣቱ በትግራይ ፖለቲካ ውስጥ እየሰፋ የመጣውን የፖለቲካ ስንጥቃት አጉልቶ የሚያሳይ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች