Friday, May 8, 2026

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeሀገራዊ ጉዳዮችየራያ ወሎ አማራ ወሰን እና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ተወያየ።

የራያ ወሎ አማራ ወሰን እና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ተወያየ።

ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም–ዞብል ፖስት ዜና!

የራያ ወሎ አማራ ወሰን እና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት አዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሰዎች ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዞብል ፖስት ገልጸዋል።

የወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴው አባላት ከአሜሪካ ኤምባሲ ፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ ጋር ተገናኝተው የተወያዩ ሲሆን የራያ ወሎ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ አባላት በወቅታዊ እና ሌሎች ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጋቸው ተነግሯል።

ከሚያዝያ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ህወሓት በጉልበት መልሶ የያዛቸውን ስድስቱ የራያ ወረዳዎችን ወቅታዊ ሁኔታ እና በሕዝቡ ላይ የሚፈጸመውን በደል አስመልክቶ የራያ ወሎ አማራ ወሰን እና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ለአሜሪካ ኤምባሲ ማስረዳቱን ለመጽሔታችን የደረሰው መረጃ ያሳያል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ ህወሓት ራያ አላማጣን፣ አላማጣ ከተማን፣ ራያ ባላን፣ ራያ ዛታን፣ ራያ ኦፍላንና ራያ ኮረምን ድጋሚ በኃይል ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ የራያ አማራዎች በህወሓት ታጣቂዎች እንደተገደሉ፣ ወዳልታወቁ ስፍራዎች ታፍነው እንደተወሰዱ፣ እንዲሁም በርካቶች በየጊዜው ድብደባ እና ዘርፊያ እንደሚደርስባቸው ከዚህ ቀደም በሰራነው የምርመራ ዘገባ ማጋላጣችን ይታወሳል።

የአሜሪካ ኤምባሲ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ በበኩላቸው፣ በራያ እና አካባቢ ያለውን ሁኔታ ጨምሮ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፌዴራል መንግሥቱ እና ህወሓት መካከል እየታዩ ያሉ ውጥረቶች እና አዳዲስ የጦርነት ስጋቶች አሜሪካን እንደሚያሳስቧት ለማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴው አባላት አስረድተዋል።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች