Friday, May 15, 2026

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeሀገራዊ ጉዳዮችየሸገር ከተማ አስተዳደር ሕጋዊ ይዞታ ያላቸውን 60 ሺህ የመሬት ባለቤቶች መሬታቸውን የመንጠቅ...

የሸገር ከተማ አስተዳደር ሕጋዊ ይዞታ ያላቸውን 60 ሺህ የመሬት ባለቤቶች መሬታቸውን የመንጠቅ እንቅስቃሴ ጀመረ።

ሐምሌ 2/2017 ዓ.ም–ዞብል ፖስት ዜና!

ከሦስት ዓመታት በፊት የተዋቀረው የሸገር ከተማ ሕጋዊ የመሬት ካርታ ይዞታ ያላቸውን 60 ሺህ የመሬት ባለቤቶች መሬታቸውን ለመንጠቅ እንቅስቃሴ መጀመሩን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዞብል ፖስት ገልጸዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ሕጋዊ ይዞታ ያላቸው የመኖሪያ ቤቶችን፣ የንግድ ህንፃዎችን፣ የኢንቨስትመንት መሬቶችን፣ እንዲሁም የፋብሪካ ቦታዎችን አጥንቶ መጨረሱንና ከባለቤቶቻቸው ለመንጠቅ እንቅስቃሴ መጀመሩን ለመጽሔታችን የደረሰው መረጃ ያሳያል።

የከተማ አስተዳደሩ ሕጋዊ ይዞታ ያላቸውን የመሬት ባለቤቶች ንብረታቸውን ለመንጠቅ እንቅስቃሴ ጀምሯል የተባለው “ሸገር ከተማ ሙሉ በሙሉ ኦሮሞን እንድትመስል እናደርጋለን” በሚል እንደሆነ የመረጃ ምንጫችን አክለው ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም የሸገር ከተማን ለመመስረት ሲባል ከ110 ሺህ በላይ ቤቶች መፍረሳቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ይሄንን ተከትሎ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው በተጠና መልኩ እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል። የዚህ ማፈናቀል ሰለባ ከሆኑት መካከል የአማራ ተወላጆች አብዛኛውን ቁጥር መያዛቸው አይዘነጋም። 

የሸገር ከተማ ሕጋዊ ይዞታ ያላቸውን የመሬት ባለቤቶችን ለመንጠቅ ጥናት ካካሄደባቸውና እንቅስቃሴ ከጀመረባቸው አካባቢዎች መካከል ቡራዩ፣ ሱሉልታ፣ ለገጣፎ፣ እና ገላን ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዙ ለዞብል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።

የከተማ አስተዳደሩ ሕጋዊ የመሬት ይዞታቸውን ለመንጠቅ ጥናት ካካሄደባቸው ቦታዎች አብዛኛዎቹ የአማራ ተወላጆች መሆናቸውን የመጽሔታችን የመረጃ ምንጭ ለዞብል ፖስት ያስረዱ ሲሆን፣ ሌሎች ኦሮሞ ያልሆኑ የመሬት ባለቤቶችም የዚሁ ተግባር ሰለባ መሆናቸው ተነግሯል።

የሸገር ከተማ አስተዳደር መሰል እንቅስቃሴዎችን የጀመረ ቢሆንም፣ የከተማዋ ነዋሪዎች እና በዙሪያው የሚገኙ የኦሮሞ ገበሬዎች በበከላችው በከተማዋ ያለው የንግድ እና የሰዎች እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በመቀዛቀዙ ምክንያት፣ ሸገር ከተማን ወደ አዲስአበባ መልሳችሁ አካልሉን የሚል ደብዳቤ ለወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ለአቶ ሽመልስ አብዲሳ ማስገባታቸውን የመረጃ ምንጫችን አያይዘው ገልጸዋል። 

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰመስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ ከሁለት ዓመታት በፊት የሸገር ከተማን ምስረታ አስመልክቶ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደው ውይይት ላይ “ሸገር ከተማን የመሰረትንበት ዋነኛው ምክንያት አዲስአበባን ለመጠበቅ ነው” ሲሉ መናገራቸው አይዘነጋም።

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች