Wednesday, April 29, 2026

INFORMING WITH FIDELITY

ለማስታወቂያ ክፍት ነው

Homeሀገራዊ ጉዳዮችየህወሓት ታጣቂዎች ወደ አፋር ክልል ዘልቀው ገብተዋል ተባለ።

የህወሓት ታጣቂዎች ወደ አፋር ክልል ዘልቀው ገብተዋል ተባለ።

ሰኔ 27/2017 ዓ.ም–ዞብል ፖስት ዜና!

የህወሓት ታጣቂዎች ዛሬ ሌሊቱን ወደ አፋር ክልል ዘልቀው መግባታቸውን ዞብል ፖስት ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው የመረጃ ምንጮች አረጋግጧል።

ታጣቂዎቹ ወደ ክልሉ ዘልቀው የገቡት በአፋር ክልል መጋሊ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወታደራዊ ስልጠና እያደረገ የሚገኘውና ብርጋዲየር ጄኔራል ገብረእግዚአብሔር በየነ የሚመሩት ራሱን “የነፃ መሬት ታጣቂ” ብሎ በሚጠራው ሌላኛው የትግራይ ታጣቂ ቡድን ላይ ጥቃት ለመፈፀም እንደሆነ ለመፅሔታችን የደረሰው መረጃ ያሳያል።

ወደ አፋር ክልል ዘልቀው የገቡት የህወሓት ታጣቂዎች በጆን መዲድ እና  በወዲ ብርሀነ ይመራል የተባለው አርሚ 43 ታጣቂዎች ሲሆኑ፣ ዛሬ ሌሊት “ቶንሳ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አቋርጠው ወደ አፋር ክልል ዘልቀው ገብተዋል ሲሉ፣ መረጃውን ለመፅሔታችን ያደረሱት ምንጮች አያይዘው ገልፀዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ በአፋር ክልል ወታደራዊ ስልጠና በማድረግ ላይ የሚገኙት የነፃ መሬት ታጣቂዎች ማክሰኞ ሰኔ 24/2017 ዓ.ም ከአፋር ክልል በመነሳት ወደ ዋጅራት ወረዳ ጥሰው ገብተው ከህወሓት ታጣቂዎች ጋር ውጊያ ማድረጋቸው ይታወሳል።

በጆን መዲድና ወዲ ብርሃነ የሚመራው አርሚ 43 ታጣቂዎች ዛሬ ሌሊት ወደ አፋር ክልል ዘልቀው የገቡት፣ ባለፈው ማክሰኞ ከአፋር ክልል በመነሳት ወደ ዋጅራት ወረዳ ጥሰው ለገቡት የነፃ መሬት ታጣቂዎች አፀፋዊ ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ ዞብል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።

የፌዴራልም ሆነ የትግራይ ክልል መንግሥት እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ የሰጡት አስተያየት ባይኖርም፣ በሁለቱ የትግራይ ታጣቂ ቡድኖች መካከል የተፈጠረው ግጭት እየተባባሰ ስለመምጣቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታዩ ያሉ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ማሳያ ናቸው። 

RELATED ARTICLES

በጣም የተወደዱ

የቅርብ ጊዜ አስተያየቶች